ሊቨርፑል ከቶተንሃም ሆትስፐር እና ማንቸስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ - የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

ሊቨርፑል ከቶተንሃም ሆትስፐር
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

ሊቨርፑል ከቶተንሃም ሆትስፐር፤ አስቶን ቪላ ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች ናቸው።

ቶተንሃም ያለፉትን 5 የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን "ቶተንሃም አሰልጣኝ ቶዶርን ካላሳናበተ በሊጉ ያለው ቆይታ አደጋ ውስጥ ይገባል" ሲል አስጠንቅቋል።

ሱተን ይህንን ጨምሮ ቀሪዎቹን የሊጉን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

በርንሌይ ከ በርንመዝ

በርንሌይ በሊጉ ለመቆየት ብዙ መሥራት እንደሚገባው ስገልጽ ብቆይም አሁን ግን የሚሳካ አይመስልም።

የስኮት ፓርከር ቡድን በቀላሉ እጅ የሚሰጥ ቡድን ባይሆንም በዚህ ጨዋታ ምንም ነጥብ አያገኝም።

ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ያልተሸነፈው በርንመዝ ከሦስት ተከታታይ አቻ ውጤት በኋላ ወደ ድል የሚሸጋገርበት ዕድል ያለ ይመስላል።

ግምት፡ 0 - 2

ሰንደርላንድ ከ ብራይተን

ሰንደርላንድ በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠ ቢመስልም በጥሩ ውጤት የውድድር ዓመቱን ለመጨረስ በሜዳው ማሸነፍ ይኖርበታል።

እየተንገዳገደ ይመስል የነበረው ብራይተንም ብሬንትፎርድ እና ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸንፎ በጠባብ ውጤት ለአርሰናል እጁን ሰጥቷል።

ብራይተን ይህንን ጨዋታ ካሸነፈ በደረጃ ሰንጠረዡ ከሰንደርላንድ በላይ ይቀመጣል።

ግምት፡ 1 - 1

አርሴናል ከ ኤቨርተን

ምስጋና ለካይ ሃቨርትዝ የመጨረሻ ደቂቃ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ይግባውና አርሴናል ደካማ በነበረበት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ከባየር ሊቨርኩሰን ጋር አቻ ተለያይቷል።

ቡድኑ የጉልበት መድከም ሊኖርበት ቢችልም የቡድን ጥልቀቱ አስተማማኝ ነው።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ጠንካራ ፉክክር አድርገው መድፈኞቹን ያሸነፉበት ታሪክ የሚደገም ይመስለኛል።

ኤቨርተን ጨዋታውን ከባድ ሊያደርገው እና ጎል ሊያስቆጥር ቢችልም ድሉ የአርሰናል ይሆናል።

ግምት፡ 2 - 0

ቼልሲ ከኒውካስል ዩናይትድ

ቼልሲ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

ቼልሲ በሜዳው ከኒውካስል ጋር ካደረጋቸው 12 ጨዋታዎች 11ዱን ማሸነፍ ችሏል።

በመጀመሪያው ዙር ሁለቱ ቡድኖች 2 አቻ መለያየታቸው ይታወሳል።

አንቶኒ ጎርደን በሙሉ ጤንነት ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ኒውካስል ተስፋ ያደርጋል።

ጎርደን ተጫወተም አልተጫወተም ግን ሦስቱ ነጥብ የሰማያዊዎቹ ነው።

ግምት፡ 2 - 1

ዌስት ሃም ከ ማንቸስተር ሲቲ

ሲቲ ከ2015 ወዲህ በዌስት ሃም ባይሸነፍም ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቀዋል።

ሲቲ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት በካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ ከአርሴናል እንዲሁም በኤፍኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ከሊቨርፑል ጋር ወሳኝ ጨዋታዎች ይጠብቁታል።

ዌስት ሃም ባለፈው ሳምንት ፉልሃምን ማሸነፍ ቢችልም በሜዳው ግን አሳማኝ ቡድን አልሆነም።

ጨዋታው ለሲቲ ከባድ ቢሆንም በአሸናፊነት ያጠናቅቃል።

ግምት፡ 1 - 2

እሑድ

ክሪስታል ፓላስ ከ ሊድስ ዩናይትድ

በመጀመሪያው ዙር ሊድ 4 ለ 1 ቢያሸንፍም ፓላስ ሁለት ጨዋታዎችን አሸንፎ ወደ ጥሩ አቋሙ በመመለሱ ጥሩ ፉክክር ይኖራል።

ሊድስ ከሊጉ የመውረድ ከፍተኛ ስጋት ስላለበት ውጤት ማስመዝገብ ይኖርበታል።

ቡድኑ ጠንካራ አቋም እንዳለው ቢያሳይም በደረጃ ሰንጠረዡ ግን ከወራጅ ቀጠና በሦስት ነጥብ ብቻ እንደሚርቅ ያሳያል።

በዚህ ጨዋታ ጎሎች እንደሚቆጠሩ ብገምትም ጨዋታው አቻ ይጠናቀቃል።

ግምት፡ 2 - 2

ማንቸስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ አስቶን ቪላ

ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጡ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ጨዋታ ነው።

ማይክል ካሪክ ቡድኑ በኒውካስል ከደረሰበት ሽንፈት ማገገሙን የሚያሳይበት ጨዋታ ይሆናል።

ቪላ የውድድሩን ዓመቱን በደካማ አቋም ጀምሮ በደካማ አቋም ሊያጠናቅቅ እየተንደረደረ ይመስላል።

በመጀመሪያው ዙር ቪላ 2 ለ 1 ቢያሽንፍም አሁን በተመሳሳይ ውጤት ዩናይድ የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

ግምት፡ 2 - 1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ፉልሃም

ይህ ለፎረስት ወሳኝ ጨዋታ ነው።

ቡድኑ ከሲቲ ጋር አቻ ቢለያይም አዲሱ አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ላለፉት 11 ጨዋታ ያላሳኩትን ድል ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል።

ይህንን አሳክተው ሦስት ነጥብ ያገኛሉ ብዬ ግን አላስብም።

ፉልሃም ምን ዓይነት ውጤት እንደሚያስመዘግብ ለማወቅ አዳጋች ቢሆንም ቡድኑ በነጻነት እንደሚጫወት ይገመታል።

ግምት፡ 1 - 1

ሊቨርፑል ከ ቶተንሃም

አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ስፐርስን ተረክበው ይበልጥ አወሳስበውታል።

ቡድኑ በውስብስ ችግሮች ውስጥ ሲሆን ቱዶር የመጡት በፍጥነት ውጤት ለማግኘት ቢሆን እየተሳካ አይደለም።

ሊቨርፑልም ቢሆን አሳማኝ ቡድን ሊሆን አልቻለም።

በዚህ ጨዋታ ግን አይሸነፉም።

ግምት፡ 2 - 0

ሰኞ

ብሬንትፎርድ ከ ዎልቭስ

ዎልቭስ ጥሩ መነሳሳት ላይ ቢሆንም ከሜዳው ውጭ ማሸነፍ ያለቻለ ብቸኛው ቡድን ነው።

ብሬንትፎርድ በአሰልጣኝ ኬት አንድሪው ስር በሊጉ ጥሩ እየተጓዘ ይገኛል።

ግምት፡ 2 - 1