አርሴናል ከ ማንቸስተር ሲቲ፡ የካራባኦ ዋንጫ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

አርሴናል ከማንቸስተር ሲቲ
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

በካራባኦ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ የሚጫወቱት አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ ክለቦች እሑድ በዌምብሌይ ስታዲየም ይፋለማሉ።

ቀሪዎቹ የሊጉ ቡድኖች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

በሊጉ ለመቆየት የሚጫወቱት ቶተንሃም እና ፎረስት እሑድ የሚያደርጉት ጨዋታ ከተጠባቂዎቹ መርሐ ግብሮች አንዱ ነው።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የካራባኦ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን እና የሊጉን መርሃ ግብሮች እንደሚከተለው ገምግሟል።

አርብ

በርንመዝ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ከበርንመዝ ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ዩናይትድ በማይክል ካሪክ ስር የተለየ ቡድን ከመምሰሉም በላይ በሻምፒዮንስ ሊግ በመሳተፍ በመጫወት ላይ ይገኛል።

በርንመዝ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ በሦስቱ ጎል አላስቆጠሩም።

ይህንንም ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚያጠናቅቁ ይመስላል።

ግምት፡ 1 - 1

ቅዳሜ

ብራይተን ከ ሊቨርፑል

የሊቨርፑልን ውጤት ለመገመት አስቸጋሪ ሆኗል።

ዘንድሮ የሊቨርፑል ውጤታማው ተጫዋች ዶምኒክ ሳቦዝላይ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ቡድኑ ውጤት ለማግኘት የሚጠብቀው እሱን ነው።

ብራይተን ካለፉት አራት ጨዋታዎች በሦስት ማሸነፍ ችሏል።

ይህንን ጨዋታ ብራይተን ያሸንፋል።

ግምት፡ 2 - 1

ፉልሃም ከ በርንሌይ

በርንሌይ ከሊጉ መውረዱ የማይቀር ቢሆንም ቡድኑ ተፎካካሪ መሆኑን ደጋግሞ አሳይቷል።

ፉልሃም ዘንድሮ ጥሩ ባይሆንም ከዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያሳካል።

ግምት፡ 2 - 0

ኤቨርተን ከቼልሲ

ኤቨርተን ከ ቼልሲ

ቼልሲ ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ሲሸነፍ ምንም መፍጠር አልቻለም ነበር።

ኤቨርተን በበኩሉ ከአርሴናል ጋር እስከመጨረሻው ቢፋለምም ከመሸነፍ አልዳነም።

ሊያም ሮዘኒየር በክልቡ ለመቆየት በቀሪ ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ በሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ አለባቸው።

ግምት፡ 1 - 1

ሊድስ ከ ብሬንትፎርድ

ሊድስ የሚጫውትበት መንግድ ለብሬንትፎርድ መልሶ ማጥቃት የተመቻቸ ነው።

ብሬንትፎርድ ባለፈው ሳምንት 2 ለ 0 ሲመራ ቆይቶ ከዎልቭስ ጋር አቻ ተለያይቷል።

ግምት፡ 2 - 1

እሑድ

ኒውካስል ከ ሰንደርላንድ

ይህ ለኒውከሳስል ወሳኝ ጨዋታ ነው። ይህንን ጨዋታ ከተሸነፉ አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ከፍተኛ ትችት ያስተናግዳሉ።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሰንደርላንድ ተሸንፈዋል።

ሰንደርላንድ በበኩሉ ባለፉት ጨዋታዎች አቋሙ ወርዷል።

ግምት፡ 2 - 0

አስቶን ቪላ ከ ዌስት ሃም

አስቶን ቪላ ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች ሲሸነፍ ዌስት ሃም ደግሞ በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ አሳይቷል።

ቪላ ሽንፈቶች ቢደጋገሙበትም አሁንም አራተኛ ደረጃን እንደያዘ ነው።

ጃሮድ ቦዌንን መቆጣጠር ከቻሉ በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማሳካት ይችላሉ።

ግምት፡ 2 - 1

ቶተንሃም ከኖቲንግሃም ፎረስት

ቶተንሃም ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ቶተንሃም ይህንን ጨዋታ ካሸነፈ በአሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ዙሪያ ያጠላው ጥላ የሚነሳበት ይሆናል።

ፎረስት በበኩሉ ጎል የማስቆጠር ችግሩን ካልቀረፈ በዚህ ጨዋታም ዋጋ ይከፍላል።

ቶተንሃም የተወሰኑ የተጎዱ ተጫዋቾች ቢኖሩትም ይህንን ጨዋታ የሚያሸንፍ ስብስብ አለው።

ግምት፡ 1 - 0

ካራባኦ ዋንጫ

አርሴናል ከማንቸስተር ሲቲ

ይህ ጨዋታ በፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ጉዞ ላይ ምንም ተጽዕኖ የሚያሳድር አይመስለኝም።

ሲቲ የትኛውንም ያህል ጠንካራ ቢሆን በሊጉ ከመድፈኞቹ ሊቀድም አይችልም።

ከሊጉ ጨዋታዎችን አንጻር ይህ ጨዋታ የተለየ እንደሚሆን እገምታለሁ።

ሁለቱም ቡድኖች በድፍረት ለመጫወት የማይሞክሩበት አሰልቺ ጨዋታ ይሆናል።

ግምት፡ 0 - 0 በመለያ ምት ሲቲ ያሸንፋል