ፖፕ ሊዮ ስለ 'አምባገነኖች' ያደረጉት ንግግር ትራምፕ ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ተናገሩ
ሊቀ ጳጳስ ሊዮ በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር "አምባገነኖች" በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ጦርነቶች ላይ እያፈሰሱ ነው ቢሉም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ ከገቡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ያደረጉት ንግግር "ፕሬዚዳንቱ ስለእኔ አስተያየት ከመስጠታቸው" ከቀናት በፊት የተጻፈ ነው ብለዋል።
"ከፕሬዚዳንቱን ጋር እንደገና ለመመላለስ እንደሞከርኩ ቢቆጠርም ይህ የእኔ ዓላማ አይደለም" ሲሉ ቅዳሜ ዕለት ወደ አንጎላ እየበረሩ በነበረበት ወቅት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት "የውጭ ፖሊሲ ላይ የከፋ" ሲሉ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን የከፈቱትን ወታደራዊ ዘመቻን ሲተቹ የነበሩትን አሜሪካዊው ሊቀ ጳጳስ ተችተዋል።
በአፍሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ፖፕ ሊዮ "ትክክል ያልሆነ የተወሰነ ትረካ" እንደተፈጠረ በመጥቀስ፣ በትራምፕ አስተያየት የተፈጠረውን "የፖለቲካ ሁኔታ" ጠቅሰዋል።
ሐሙስ ዕለት በካሜሩን ባደረጉት ንግግር "በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለግድያ እና ለውድመት ሲውል እንዳላየ የሚያልፉ መሪዎች፤ ለጤና፣ ለትምህርት እና ለግንባታ ሀብት እንደሚያስፈልግ ግን ዘንግተዋል" ብለዋል።
"የጦርነት ጌቶች ለማጥፋት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚፈጅ እንደማያውቁ ያስመስላሉ፤ ለመገንባት ግን ዕድሜ ልክም በቂ አይደለም" ሲሉ አክለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ለአስር ዓመታት ያህል ግጭት በሰፈነበት የካሜሩን "ደም የተበከለ" ክልል ውስጥ "ማለቂያ የሌለው የውድመት እና የሞት አዙሪት መኖሩን" አውግዘዋል።
አስተያየቶቹ ትራምፕን የሚመለከቱ ናቸው ብለው አንዳንዶች የተረጎሙት ሲሆን ፕሬዝዳንቱም በኋላ ላይ ለጋዜጠኞች "ሊቃነ ጳጳሱ የፈለጉትን መናገር ይችላሉ፤ የፈለጉትን እንዲናገሩ ብፈልግም ግን አልስማማም" ብለዋል።
የካቶሊክ ቤተክርስቲያኑ መሪ ትችት የተሞላበት ረዥም ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰነዘረባቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን "ሥልጣኔ እንደሚያወድሙ" መዛታቸውን ከኮነኑ በኋላ ነበር።
ትራምፕ የሊቀ ጳጳሱ "አድናቂ" እንዳልሆኑ እና "በወንጀል ደካማ እና የውጭ ፖሊሲ ላይ የከፋ" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።
ትራምፕ ራሳቸውን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አድርጎ የሚያሳይ ምሥል በቱሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ማጋራታቸው ተቃውሞ ካስነሳባቸው በኋላ ከገጻቸው አጥፍተዋል። ምስሉ በሠው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የተሰራው ነው።
የካቶሊክ መሪው የአፍሪካ ጉብኝት በአራት አገሮች ውስጥ በሚገኙ 11 ከተሞችን ያካትታል። ባለፈው ዓመት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ሁለተኛው ትልቁ የውጭ ጉብኝታቸው ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ የካቶሊክ እምነትን አስፈላጊነት ያንፀባርቃል ተብሏል።
ከዓለም ካቶሊኮች ውስጥ ከአንድ አምስተኛ በላይ የሚሆኑት 288 ሚሊዮን ገደማ የእምነቱ ተከታዮች በአፍሪካ ይኖራሉ ሲሉ የ2024 አሃዞች አመልክተዋል።
እንዳያመልጥዎ
ከየፈርጁ
በስፋት የተነበቡ
የሚፈልጉት ይዘት የለም