单元 2: Essential English Conversation
选择一个单元
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
课程 47
Listen to find out how to choose an activity with someone.
ከአንድ ሰው ጋር የሚያደርጉትን ድርጊት ወይንም እንቅስቃሴ እንዴት መምረጥ እንደሚቻል ለመረዳት የሚከተለውን ያዳምጡ።
练习题 1
What should we do?
Listen to find out how to choose an activity with someone.
ከአንድ ሰው ጋር የሚያደርጉትን ድርጊት ወይንም እንቅስቃሴ እንዴት መምረጥ እንደሚቻል ለመረዳት የሚከተለውን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ሁሉም የእንግሊዝኛ ተማሪ ማወቅ ያለበትን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል ስለ ዕቅድ እና አንዳንድ ነገሮች ለማከናወን ሁኔታዎችን ስለማመቻቸት እንዴት ማውራት እንደሚቻል ይማራሉ።
ክሪስ እና ፔኒ ዛሬ ለመገናኘት ወስነዋል። ተገናኝተው ምን ለማድረግ ወጥነዋል? መልሱን ለማወቅ ውይይታቸውን ያዳምጡ።
Chris
What should we do?
Penny
Why don't we go shopping?
Chris
I don't want to go shopping. Why don't we go swimming instead?
Penny
OK! That sounds good!
ምህረተስላሴ
ንግግራቸውን ካልተረዱት አያስቡ። ውይይቱን እንከፋፍለውና ደግመው እንዲሉት ጊዜ እንሰጥዎታለን።
What should we do?
ምህረተስላሴ
ፔኒ የመገብየት 'go shopping' ኃሳብ ሰነዘረች። ይሄንን ለመጠቆምም 'why don't we…?'ን ተጠቅማለች።
Why don't we go shopping?
ምህረተስላሴ
'Why don't we…?' የሚለውን ሐረግ በመጠቀም ሌሎች ተግባሮችን መጠቆምም እንችላለን። ተግባሩን ከሐረጉ በኋላ እናስከትላለን። 'eat in a restaurant' ምግብ ቤት ውስጥ መብላት ወይም 'play football' እግር ኳስ መጫወትን መጠቆም ይችላሉ።
Why don't we eat in a restaurant?
Why don't we play football?
ምህረተስላሴ
ክሪስ ገበያ መሄድ ስለማይፈልግ 'I don't want to…' ብሏል።
I don't want to go shopping.
ምህረተስላሴ
አዲስ ድርጊትን ለመጠቆም ለምን አናረግም የተሰኘ ሐረግ ተጠቅሟል። ድርጊቱ ዋና መዋኘት 'go swimming' ነው። ሰዎች ብዙ ጊዜ ከ'don't' በኋላ በአረፍተ ነገሩ መቋጫ ላይ 'instead'ን ያስገባሉ። ይህም ያቀረቡትን አማራጭ ለመግለፅ ነው።
Why don't we go swimming instead?
ምህረተስላሴ
ፔኒ ሀሳቡን ስለወደደችው፤ እሺ፣ ጥሩ ኃሳብ ይመስላል ብላለች።
OK! That sounds good!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሶፊያ እና ፖል ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲወያዩ በማዳመጥ የተማሩትን ይከልሱ። ምን ለማድረግ ወሰኑ?
Sophie
What should we do?
Paul
Why don't we go to the cinema?
Sophie
OK. Why don't we go to the café afterwards?
Paul
OK! That sounds great!
ምህረተስላሴ
ፖል ወደ 'the cinema' ሲኒማ መሄድ ፈልጓል። ይሄንንም 'why don't we…?' የሚለውን ሐረግ በመጠቀም ገልጿል።
Why don't we go to the cinema?
ምህረተስላሴ
ሶፊ በሀሳቡ ተስማማች። ተጨማሪ ድርጊት 'going to the cafe' ወደ ካፌ መሄድንም ጠቆመች። ይህንንም ከሲኒማ በኋላ 'afterwards' እንደሚያደርጉት ገልጻለች።
Why don't we go to the café afterwards?
Why don't we go to the café before?
ምህረተስላሴ
ፖል 'great' በጣም ጥሩ ኃሳብ ነው ሲል ተስማማ።
እሺ፤ እስኪ ደግመን እንሞክረው። እንግሊዝኛውን ሰምተው ደግመው ይበሉ።
What should we do?
Why don't we go shopping?
I don't want to go shopping.
Why don't we go swimming instead?
OK! That sounds good!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱት እንይ እስኪ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ምን እናድርግ?
What should we do?
ለምን ገበያ እንሄድም?
Why don't we go shopping?
ገበያ መሄድ አልገልግም።
I don't want to go shopping.
ገበያውን ትተን ለምን አንዋኝም?
Why don't we go swimming instead?
እሺ። እሱ ጥሩ ኃሳብ ይመስላል።
OK! That sounds good!
ምህረተስላሴ
ግሩም! አሁን ደግሞ ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ ለክሪስ በመናገር ልምምድ ያድርጉ። በሃሳብዎ ካልተስማማ፤ እሱ ማድረግ የሚፈለገውን ይቀበሉ። ትሁት ለመሆን 'that sounds good! ማለት አይርሱ።
What should we do?
Why don't we go swimming instead?
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ። አሁን ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ በእንግሊዝኛ መግለጽ ችለዋል። ከጓደኛዎ ጋር የተማሩትን ይለማመዱ።አብረውን ስለነበሩ እናመሰግናለን። ለተጨማሪ Essential English በሚቀጥለው ዝግጅታችን ይጠብቁን።
Listen to find out how to choose an activity with someone.
ከአንድ ሰው ጋር የሚያደርጉትን ድርጊት ወይንም እንቅስቃሴ እንዴት መምረጥ እንደሚቻል ለመረዳት የሚከተለውን ያዳምጡ።
What should we do?
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
帮助
练习题
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
提示
ጥያቄ ስናቀርብ የምንጠቀመውን ቃል ያስታውሱ።Question 1 of 3
帮助
练习题
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
提示
ሌላ ነገር ለመጠቆም አሉታዊ ጥያቄዎችን እንጠቀማለን።Question 2 of 3
帮助
练习题
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ።
提示
የተለየ አማራጭን ለመጠቆም በጥያቄው መጨረሻ ላይ የምናስገባው ቃል የትኛው ነው?Question 3 of 3
Excellent! 太棒了! Bad luck! 加分:
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዷችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
本课词汇
What should we do?
ምን እናድርግ?
Why don’t we_____?
ለምን ______ አናደርግም?
Why don't we ______ instead?
ከእርሱ ይልቅ ለምን ______ አናደርግም?
go shopping
ወደ ገበያ መሄድ
go swimming
ወደ ዋና መሄድ
go to the cinema
ወደ ሲኒማ ቤት መሄድ
eat in a restaurant
ምግብ ቤት ውስጥ መመገብ
play football
እግር ኳስ መጫዎት
afterwards
ከዚያ በኋላ
before
ከዚያ ቀድሞ/በፊት
That sounds good!
ጥሩ ኃሳብ ነው/ይመስላል