ኮሮናቫይረስ፡ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስችሉ ቀላል ተግባራዊ ስልቶች

እራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ከምንከላከልባቸው መንገዶች አንዱ ማኅበራዊ ርቃታችንን በመጠበቅ ነው።

አገራት እና ግለሰቦች ሰዎች ማኅበራዊ ርቀታቸውን መጠበቅ የሚያስችሏቸውን ተግባሯዊ ዘዴዎችን አምጥተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ይህ አሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ነው። ሰዎች እራሳቸውን ዘና ለማድረግ ወደ መናፈሻዎች ሲሄዱ መቀመጥ ሚችሉት በክቦቹ ውስጥ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በስሪ ላንካ ሰዎች በአሳንስር (ሊፍት) ውስጥ በዚህ መልኩ ርቃታቸውን በመጠበቅ እራሳቸውን ከቫይረሱ ይከላከላሉ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኝ ምግብ ቤት መመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ካርቶን ላይ የተሳሉ ስዕሎት ይቀመጣሉ። ተጠቃሚዎች መቀመጥ የሚችሉት በባዶ ወንበሮች ላይ ነው። የስዕሎቹ መኖር ምግብ ቤቱ በሰው የተሞላ አይነት ስሜት እንዲፈጥር ያደርጋል ተብሎለታል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ሰዎች ታይላንድ ባንኮክ በሚገኝ በዚህ ምግብ ቤት ውስጥ ምሳ እየተመገቡ ነው። በሰዎች መካከል የተዘረጉት የላስቲክ መከለያዎች ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸውን ዝቅ ያደርጋሉ።

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, የአልባኒያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበራዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ የተቀመጠላቸውን አቅጣጫ በመከተል ወደ ህንጻ ሲገቡ።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ይህ ደግሞ ሂውስተን ቴክሳስ ነው። ይህ የሴቶች የውበት ሳሎን በዚህ መልኩ ደንበኞቹን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይጥራል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ይህ ምስል ብራሰልስ ቤልጄም የሚገኙ ተማሪዎች ርቀታቸውን በመጠበቅ ሲነጋገሩ ያሳያል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በፈረንሳይ ሰዎች ባቡር ሲጠብቁ ርቀታቸውን ጠብቀው ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የአሜሪካ መንግሥት በሳን ፍራንሲስኮ ቤት አልባ ለሆኑ ዜጎች ያዘጋጀው ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ ርቀትን በጠበቀ መልኩ የተዘጋጅቷል ነው።

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በባንኮክ ታይላንድ የሚገኝ ምግብ ቤት፤ ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠበቁ ለማስገደድ 'ፓንዳ' አሻንጉሊት በየወንበሮቹ ላይ አስቀምጧል። ሰዎች አሻንጉሊቱን አንስተው መቀመጥ አይችሉም። በዚህም ማኅበራዊ ርቀንት ማስጠበቅ ተችሏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በስፔን ማድሪድ ሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ምዕመናን ብቻ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይፈቅዳል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በሚላን ጣሊያን በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ አስተናጋጁ የደንበኛውን የሰውነት ሙቀት ሲለካ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሌባኖስ ቤይሩት በሚገኝ መስጅድ ውስጥ፤ ሙስሊሞች ጸሎት ሲያካሂዱ በዚህ መልኩ ርቀታቸውን በመጠበቅ ነው። በመስገጃ ምንጣፉ ላይ የተቀረጸው ስዕል ሰዎች ርቀታቸውን በቀላሉ እንዲያውቁ ያስችላል።

የሁሉም ፎቶግራፎች የባለቤትነት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።