የግብፅ መካነ መቃብር፡ ሳቃራ ፒራሚድ ኮምፕሌክስ አቅራቢያ አዲስ ግኝት ይፋ ተደርጓል

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባለሙያዎች በጣም የተለየና ተጠብቆ የቆየ ያሉትን መካነ መቃብር ጋዜጠኞች ገብተው እንዲያዩ ተፈቅዶላቸው ነበር።

በግብፅ ቄሶች ያረፉበትና ላለፉት 4400 ዓመታት ተነክቶ የማያውቅ መካነ መቃብር ማግኘታቸውን አርኪዮሎጂስቶች አስታወቁ።

በግብፅ የአንቲኪዩቲስ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ የሆኑት ሙስጠፋ ዋዚሪ ባለፉት አስርት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ አስደናቂ ግኝት ነው ሲሉ ገልፀውታል።

በካይሮ አቅራቢያ ሳቃራ ፒራሚድ የተገኘው ይህ መካነ መቃብር በቀለማት ያሸበረቁ ሥዕላዊ መግለጫዎች፣ የፈርኦን ሐውልቶች እንዲሁም ዋህትይ የተባሉት የንጉሣዊ ቄስ ከእናታቸው፣ ከሚስታቸው እና ከዘመዶቻቸው ጋር በሚያሳይ ምስል የተሞላ ነው።

አርኪዮሎጂስቶች የመካነ መቃብሩ ባለቤት የመቃብር ክዳን ማግኘታቸውን ተከትሎ ሌሎች አዳዲስ ግኝቶችን ለመፈለግ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 16 ቁፋሮ መጀመራቸው ታውቋል።

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የግብፅ ፒራሚድ በሚገኝበት ሳቃራ ጥንታዊው ኔክሮፖሊስ ሰፊው መካነ መቃብር የተገኘበት ቦታ

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የመካነ መቃብሩ ውጫዊ ክፍል የሚያሳየው በድንጋይ የተሰራውን ረዥም ግድግዳ

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በጥንታዊ የግብፅ ጽሁፍ እንዲሁም በሥዕላዊ መግለጫዎች የተሸፈነው መካነ መቃብር

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በመካነ መቃብሩ ላይ የተሰሩ የሰዎች ሐውልት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, የቁፋሮው ፕሮጀክት መሪ የሆኑት ሙስጠፋ አብዶ፤ መካነ መቃብሩ 10 ሜትር ርዝመት፣ 3ሜትር ስፋትና 3ሜትር ከፍታ አለው

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በጥንታዊቷ ግብፅ ቄሶች ልዩ ክብር ይሰጣቸው ነበር

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, የመካነ መቃብሩ ቀለም ላለፉት 4400 ዓመታት በጥሩ ሁኔታ ይገኛል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 2500 - 2350 ድረስ ግብፅን ሲመሩ የነበሩት ዋህቲይ ሐውልት

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, ዋናውን ቄስና ቤተሰቦቹን የሚያሳየው በቀለም ያጌጠው ግድግዳ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, አርኪዮሎጂስቶች መካነ መቃብሩ ላይ ተጨማሪ ምርምር ለማድረግ አቅደዋል።