የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ሴት ፕሬዝዳንት ይሆናሉ ተብለው የነበሩት የካማላ ሃሪስ ሕይወት በምሥሎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የንባብ ጊዜ: 4 ደቂቃ

በተጠናቀቀው የአሜሪካ ምርጫ ላይ አዲስ ታሪክ ያስመዘግባሉ ተብለው ተጠብቀው የነበሩት ካማላ ሃሪስ ድል ሳይቀናቸው በዶናልድ ትራምፕ ተሸንፈው ተሰናብተዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንት ሃሪስ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንጻር በብዙ መልኩ የተሻሉ ሆነው የመመረጥ ዕድል ይኖራቸዋል በሚል በርካቶች ቢጠብቁም አብላጫው መራጮች ድምጻቸውን ለትራምፕ ሰጥተዋል።

የመጀመሪያዋ ሴት፣ ጥቁር እና የሕንድ ዝርያ ያላቸው ድርብርብ ታሪክ በማስመዝገብ ወደ ኃያሏ አገር የመሪነት መንበር ይመጣሉ ቢባልም ሁሉም በነበር ቀርቷል።

የፎቶው ባለመብት, Kamala Harris / X

የምስሉ መግለጫ, ጨቅላዋ ሃሪስ እና እናቷ ሽያማላ

ካማላ ዴቪ ሃሪስ ስደተኛ ከሆኑት ወላጆቻቸው ከትውልደ ሕንዳዊቷ እናታቸው ሽያማላ እና ትውልደ ጃማይካዊ ከሆኑት አባቷ ዶናልድ በካሊፎርኒያ ግዛት ኦክላንድ ውስጥ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 20/1964 ነው የተወለዱት። ካማላ ማያ የተባለች ታናሽ እህት አለቻቸው።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ታዳጊዋ ሃሪስ

የካማላ አባት በስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ ኃላፊነት ካገኙ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ካማላ ሰባት ዓመት እያሉ ነበር ወላጆቻቸው ፍቺ የፈጸሙት። ሁለቱ ሴት ልጆችም ጊዜያቸው ለሁለት ተከፍሎ ከተለያዩት ወላጆቻቸው ጋር ያሳልፉ ነበር።

የካማላ ሁለቱም ወላጆች በሰብአዊ መብቶች መከበር እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳታፊዎች ስለነበሩ፤ ካማላም ገና በለጋ ዕድሜያቸው ተመሳሳይ አመለካከት እንዲያራምዱ ረድቷቸዋል።

ካማላ በአሜሪካ ውስጥ ካሉ በታሪክ የጥቁሮች ናቸው ከሚባሉ ቀዳሚ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካል ሳይነስ እና ኢኮኖሚክስት አጥንተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Kamala Harris / X

የምስሉ መግለጫ, ወጣቷ ሃሪስ (ከቀኝ) ከጓደኛዋ ጋር በመብቶች ሰልፍ ላይ

የፎቶው ባለመብት, Karen Gibbs

የምስሉ መግለጫ, ወጣቷ ሃሪስ (ከግራ ሁለተኛ) ከሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ጓደኞቿ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Kamala Harris / X

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ ከዩኒቨርስቲ በተመረቀችበት ወቅት

በአውሮፓውያኑ 1990 ሃሪስ ከዩኒቨርስቲ ከወጡ በኋላ በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ዐቃቤ ሕግ በመሆን ነበር ሥራ የጀመሩት። በመጀመሪያ አላሜዳ በተባለው አካባቢ ዐቃቤ ሕግ የነበሩ ሲሆን፣ በኋላ ደግሞ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ዞረዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ የአላሜዳ ዐቃቤ ሕግ በነበረችበት ጊዜ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ በጋዜጠኞች ተከባ

በ2011 ደግሞ በአሜሪካ በሕዝብ ብዛቷ ቀዳሚ የሆነችው የካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው ሲመረጡ፣ የመጀመሪያዋ ሴት እና ጥቁር ለመሆን በቅተዋል።

በተጨማሪም የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት እና የተያያዥ ጉዳዮች መብቶች እንቅስቃሴ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ መሪ የነበሩ ሲሆን፣ በግዛቲቱ የመጀመሪያውን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን እንዲካሄድ አድርገዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ እና ባለቤቷ

ሃሪስ በአውሮፓውያኑ 2013 በጓደኞቻቸው አማካኝነት ከዳግ ኤምሆፍ ጋር ከተዋወቁ ከዓመት በኋላ ጋብቻ መሥርተዋል። ሃሪስ ልጆች ባይኖሯቸውም የባለቤታቸው ኤምሆፍ ሁለት ልጆች የእንጀራ እናት ናት።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ እና ባለቤቷ

በዐቃቤ ሕግነት በሠሩባቸው ጊዜያት ያሳዩት ጽኑ የሕግ አቋም ወደ ፖለቲካው መድረክ እንዲሸጋገሩ በር ከፍቶላቸዋል። በአውሮፓውያኑ ደግሞ 2017 ለካሊፎርኒያ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነት ተመርጠዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ በሴኔት አባልነታቸው ወቅት

ሃሪስ በ2020 ላይ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ቢቀርቡም የምታራምዱትን ርዕዮተ ዓለም እና የፖሊሲ አማራጭ በአግባቡ ለማቅረብ ችግር ስለገጠማቸው ብዙም አልገፉበትም። ነገር ግን የጆ ባይደን ምክትል በመሆን በምርጫው ውስጥ ቀጥለው ለአሸናፊነት በቅተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ ከባይደን ጋር

ባይደን ትራምፕን በማሸነፍ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፣ ሃሪስ የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታን በመያዝ የመጀመሪያዋ ሴት፣ ጥቁር ሴት፣ እና የደቡብ እስያ ዝርያ ያላቸው በመሆን ቦታውን ለመያዝ ችለዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ

ሃሪስ በምክትል ፕሬዝዳንትነት አሜሪካ እና ሜክሲኮ በሚዋሰኑበት ድንበር በኩል የሚጎርፉትን ስደተኞችን የመቆጣጠር ኃላፊነት ቢሰጣቸውም በቂ ሥራ አልሠሩም በሚል ሲተቹ ቆይተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ የድንበር አካባቢን ሲጎበኙ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በጽንስ ማቋረጥ መብት ላይ ትኩረት የሚያደርጉት ሃሪስ ቀደም ሲል ከነበሩ ፕሬዝዳንቶችም ሆነ ምክትል ፕሬዝዳንቶች በተለየ በሥልጣን ዘመናቸው የጽንስ ማቋረጫ ክሊኒክን በመጎብኘት የመጀመሪያዋ ሆነዋል።

ለ2024 ምርጫ የዲሞክራቶች ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት ጆ ባይደን በዕድሜ መግፋት ምክንያት እራሳቸውን በድንገት ከፉክክሩ ሲያገሉ ሃሪስ ባልተጠበቀ ሁኔታ ዕጩ ፕሬዝዳንት ሆነው የመቅረብ ዕድል አግኝተው ነበረ።

በአጭር ጊዜ ውስጥም ዲሞክራቶች የፓርቲያቸው አዲስ ተስፋ የሆኑትን ካማላ ሃሪስ ዕጩ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በመደገፍ የምርጫ ዘመቻውን አጧጡፈውት የቆዩ ቢሆንም ለማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ በምክትል ፕሬዝዳንትነት አብረዋቸው የተወዳደሩት ቲም ዋልዝ ጋር

ለምርጫ ቅስቀሳ ከአንድ ግዛት ወደ ሌላ ግዛት፣ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ እየከነፉ የነበሩት ሃሪስ በጥቅምት ወር 60ኛ የልደት በዓላቸውን አውሮፕላን ላይ ነበር ያከበሩት።

ሃሪስ በዘንድሮው ምርጫ ማሸነፍ ቢችሉ ኖሮ በድጋሚ በበርካታ መልኩ በአሜሪካ ታሪክ ላይ ስማቸው እንዲሰፍር ማድረግ ይችሉ ነበር።

ካማላ ሃሪስ በዶናልድ ትራምፕ በማያሻማ ሁኔታ ባይሸነፉ እና የአሜሪካውያንን ይሁንታ ቢያገኙ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት፣ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ፕሬዝዳንት እና የመጀመሪያዋ የሕንድ ዝርያ ያላቸው ፕሬዝዳንት ለመሆን ይችሉ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ሃሪስ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ፎቶ እየተነሱ