Essential English Conversation :1 واحد
انتخاب واحد
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
جلسه 11
Listen to find out how to ask someone how many brothers and sisters they have.
አንድ ሰው ስንት ወንድሞች እንዳሉት እንዴት እንደሚጠየቅ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Session 11 score
0 / 3
- 0 / 3تمرین 1
تمرین 1
How many brothers and sisters do you have?
Listen to find out how to ask someone how many brothers and sisters they have.
አንድ ሰው ስንት ወንድሞች እንዳሉት እንዴት እንደሚጠየቅ ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

Local presenter
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይችላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation እነኳን በደህና መጡ። ምህረት እባላለሁ። በዚህ ክፍል ሰዎች ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ይማራሉ።
እስኪ ሁለት ሰዎች ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው ሲጠያየቁ ያዳምጡ።
Donna
How many brothers and sisters do you have?
Ray
I have one brother. How about you?
Donna
I don’t have any brothers and sisters.
Local presenter
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ዶና ሬይን ‘ስንት ወንድሞች እና እህቶች አሉህ?’ ‘How many brothers and sisters do you have?’ ስትል ጠየቀችው። ‘how many…do you have?’ የሚለውን ሐረግ የምንጠቀምበት ሰዎች የአንድ ነገር ምን ያህል እንዳላቸው ለመጠየቅ ነው። በውይይቱ ውስጥ የነበረው የመጀመሪያው ጥያቄ ይሄው። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
How many brothers and sisters do you have?
Local presenter
ከዚያ ሬይ ‘አንድ ወንድም አለኝ’ ‘I have one brother’ በማለት ምላሽ ሰጠ። ከዚያ ተመሳሳዩን ጥያቄ ለማቅረብ ‘አንችስ?’ ‘how about you?’ የሚል ቀጣይ ጥያቄ አስከተለ። ያዳምጡና ሐረጉን ይድገሙ።
I have one brother.
How about you?
Local presenter
ከዚያም ዶና ‘ምንም እህትና ወንድም የለኝም’ ‘I don’t have any brothers and sisters’ ብላ መለሰች። ‘any’ የተባለውን ቃል የምንጠቀመው ‘I don’t have…’ ስንል ነው። ሐረጉን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I don’t have any brothers and sisters.
Local presenter
በጣም ጥሩ- አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለእህቶቻቸው እና ወንድሞቻቸው ሲጠያየቁ በማዳመጥ እርሶ ያሉትን ነገር ያመሳክሩ።
How many brothers and sisters do you have?
I have one brother. How about you?
I have one brother and one sister.
How many brothers and sisters do you have?
I don’t have any brothers and sisters. How about you?
I have two sisters.
Local presenter
እሺ፥ እንደገና እንሞክር። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገራቱን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንደቸውን አንዳንድ ጊዜ ይሰማሉ።
How many brothers and sisters do you have?
I have one brother.
How about you?
I don’t have any brothers and sisters.
Local presenter
በጣም ጥሩ! እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱ እንይ እስኪ። አረፍተ ነገራቱን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ስንት ወንድሞች እና እህቶች አሉህ?
How many brothers and sisters do you have?
አንድ ወንድም አለኝ።
I have one brother.
አንችስ?
How about you?
ምንም ወንድምና እህት የለኝም።
I don’t have any brothers and sisters.
Local presenter
በጣም ግሩም - እሺ፥ አሁን ሰዎች ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል አውቀዋል። ለዶና ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ። ‘አንችስ?’ ‘how about you?’ የሚለውን ቀጣይ ጥያቄ መሰንዘርን እንዳይረሱ።
How many brothers and sisters do you have?
I don’t have any brothers and sisters.
Local presenter
በጣም ጥሩ! አሁን ጠቅላላውን ውይይት ዳግም ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Donna
How many brothers and sisters do you have?
Ray
I have one brother. How about you?
Donna
I don’t have any brothers and sisters.
Local presenter
በጣም ጥሩ! አሁን በእንግሊዝኛ ሰዎች ምን ያህል ወንድሞች እና እህቶች እንዳሏቸው መጠየቅ ይችላሉ። የተማሩትን ነገር መለማመድን አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈለጉና ‘ምን ያህል. . . አለህ/አለሽ?’ በማለት ይጠይቋቸው። ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
How many brothers and sisters do you have?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Help
تمرین
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ሰዎች ስንት ወንድምና እህቶች እንዳሏቸው የሚጠይቁት እንዴት ነው?Question 1 of 3
Help
تمرین
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ይህ መልስ ስንት ወንድሞች እና እህቶች እንዳሉህ ለሰዎች የሚገልፅ መሆን አለበት።Question 2 of 3
Help
تمرین
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
Hint
ከአሉታዊ አረፍተ ነገር ጋር ምንን እንጠቀማለን?Question 3 of 3
Excellent! آفرین! نمره شما Bad luck! :
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
واژه های تازه این جلسه
How many ______ do you have?
ስንት ______ አለህ?
I have one brother.
አንድ ወንድም አለኝ።
I have two sisters.
ሁለት እህቶች አሉኝ።
I don’t have any brothers or sisters.
ምንም ወንድም እና እህት የለኝም።
How about you?
አንችስ?/አንተስ?