Unit 2: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 44
Listen to find out how to ask where and when a bus leaves.
አውቶብስ የት እና መቼ እንደሚነሳ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Activity 1
At the bus station
Listen to find out how to ask where and when a bus leaves.
አውቶብስ መቼ እና የት እንደሚነሳ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ያዳምጡና መልመጃውን ይመልሱ።

ምህረተስላሴ
ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊያውቃቸው የሚገቡ የቋንቋ መሰረታዊያን ወደምናቀርብበት Essential English Conversation እንኳን በደህና መጡ። ምህረተስላሴ እባላለሁ። በዚህ ክፍል በአውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ እንዴት መረጃ እንደሚጠየቅ ይማራሉ።
በመጀመሪያ በአውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ የተደረገ ንግግር ያዳምጡ።
Sian
Where does the bus to Manchester go from?
Phil
From stop seventeen, next to the shop. It goes in ten minutes.
ምህረተስላሴ
ንግግሩን ካልተረዱት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ወደ ማንቼስተር የሚያመራው አውቶብስ የሚነሳው የት እንደሆነ ነው የጠየቀችው። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
Where does the bus to Manchester go from?
ምህረተስላሴ
ሁለተኛው ተናጋሪ ከአስራ ሰባት ቁጥር ማቆሚያ 'stop' እንደሚነሳ ነገሯታል። ከሱቁ 'the shop' ቀጥሎ 'next to' እንደሚገኝም ጨምሮ ገልፆላታል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
From stop seventeen, next to the shop.
ምህረተስላሴ
ከደረጃዎቹ 'stairs'፣ ከመግቢያው 'entrance'፣ ከመፀዳጃ ቤቶቹ 'toilets' ቀጥሎ ስለሚገኝ መነሻም ማውራት ይችላሉ።
From stop twelve, next to the stairs.
From stop thirteen, next to the entrance.
From stop fourteen, next to the toilets.
ምህረተስላሴ
ከዚያ ሁለተኛው ተናጋሪ አውቶብሱ በአስር ደቂቃ 'ten minutes' ይነሳል ብሏል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
It goes in ten minutes!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ሰዎች ወደተለያዩ ቦታዎች ለመሄድ ትኬት ሲገዙ በማዳመጥ እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
ማርክ ወደ በርሚንግሃም ሊሄድ ነው። ከመፀዳጃ ቤቶቹ 'toilets' ቀጥሎ ከሚገኘው ማቆሚያ የሚነሳውን አውቶብስ በአስራ አምስት ደቂቃ ውስጥ መያዝ ይኖርበታል።
Where does the bus to Birmingham go from?
From stop 10, next to the toilets. It goes in fifteen minutes.
አንድሬያ ወደ ብሪስትል ነው የምትሄደው። ከመግቢያው 'entrance' አጠገብ ከሚገኘው መነሻ ቁጥር ሦስት የሚነሳውን አውቶብስ በአምስት ደቂቃ ውስጥ መያዝ አለባት።
Where does the bus to Bristol go from?
From stop three, next to the entrance. It goes in five minutes.
ምህረተስላሴ
እሺ፤ አሁን ንግግሩን ደግመን እንሞክረው። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን ሁለት ጊዜ ያዳምጧቸዋል።
Where does the bus to Manchester go from?
Where does the bus to Manchester go from?
From stop seventeen, next to the shop.
From stop seventeen, next to the shop.
It goes in ten minutes.
It goes in ten minutes.
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ ትርጉማቸውን ይበሉ።
ወደማንቼስተር የሚሄደው አውቶብስ የሚነሳው ከየት ነው?
Where does the bus to Manchester go from?
ከሱቁ ቀጥሎ ካለው የመነሻ ቁጥር አስራ ሰባት
From stop seventeen, next to the shop.
በአስር ደቂቃ ውስጥ ይነሳል
It goes in ten minutes.
ምህረተስላሴ
በጣም ግሩም፤ አሁን የአውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ መረጃ መጠየቅና መስጠት ተምረዋል። ምን ልርዳዎ? እያለ ለሚጠይቀው የመጀመሪያው ተናጋሪ ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ።
How can I help you?
From stop seventeen. Next to the shop. It goes in ten minutes!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን ጠቅላላውን ውይይት አንዴ ያዳምጡና መልስዎን ያመሳክሩ።
Sian
Where does the bus to Manchester go from?
Phil
From stop seventeen, next to the shop. It goes in ten minutes!
ምህረተስላሴ
በጣም ጥሩ፤ አሁን አውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ በእንግሊዝኛ መረጃ መጠየቅና መስጠት ችለዋል። የተማሩትን መለማመድ አይርሱ። ጓደኛ ፈልገው ስለ አውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ በእንግሊዝኛ መረጃ በመጠየቅና በመመለስ ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ የኢንሴንሻል እንግሊሽ መሰናዶ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ሰላም ሁኑ!
Check what you’ve learned by putting the words in the correct order.
ቃላቱን በትክክለኛ ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
የአውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ
3 Questions
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ፍንጭ
የመጀመሪያው ቃል ‘Where’ ነው።Question 1 of 3
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ፍንጭ
የመጀመሪያው ቃል ‘From’ ነው።Question 2 of 3
ድጋፍ
Activity
Put the words in the correct order.
ቃላቱን በቅደም ተከተል ያስቀምጡ።
ፍንጭ
የመጀመሪያው ቃል ‘It’ ነው።Question 3 of 3
Excellent! Great job! መጥፎ እድል ነጥብ አስመዝግበዋል :
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ ኢሴንሻል ኢንግሊሽ መሰናዷችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
Where does the bus to ______ go from?
ወደ ______ የሚሄደው አውቶብስ የሚነሳው ከየት ነው?From platform ______.
ከመነሻ ነጥብ ______.Next to the shop.
ከሱቁ ቀጥሎIt goes in ______ minutes.
በ ______ ደቂቃ ውስጥ ይነሳል።