Unit 1: Essential English Conversation
Select a unit
- 1 Essential English Conversation
- 2 Essential English Conversation
- 3 Unit 3
- 4 Unit 4
- 5 Unit 5
- 6 Unit 6
- 7 Unit 7
- 8 Unit 8
- 9 Unit 9
- 10 Unit 10
- 11 Unit 11
- 12 Unit 12
- 13 Unit 13
- 14 Unit 14
- 15 Unit 15
- 16 Unit 16
- 17 Unit 17
- 18 Unit 18
- 19 Unit 19
- 20 Unit 20
- 21 Unit 21
- 22 Unit 22
- 23 Unit 23
- 24 Unit 24
- 25 Unit 25
- 26 Unit 26
- 27 Unit 27
- 28 Unit 28
- 29 Unit 29
- 30 Unit 30
- 31 Unit 31
- 32 Unit 32
- 33 Unit 33
- 34 Unit 34
- 35 Unit 35
- 36 Unit 36
- 37 Unit 37
- 38 Unit 38
- 39 Unit 39
- 40 Unit 40
Session 8
Listen to find out how to ask how old somebody is.
የአንድን ሰው ዕድሜ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
ክፍለጊዜያት 8 ነጥብ።
0 / 3
- 0 / 3Activity 1
Activity 1
How old are you?
Listen to find out how to ask how old somebody is.
የአንድን ሰው ዕድሜ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ለማወቅ ይሄንን ያዳምጡ።
Listen to the audio and take the quiz. ድምጹን ያዳምጡና መልመጃውን ይሞክሩ።

ጤና ይስጥልን። ማንኛውም የእንግሊዝኛ ተማሪ ሊተዋቸው የማይቻላቸውን የቋንቋ መሰረታዊያን ወደሚያቀርበው Essential English Conversation በደህና መጡ። ሐና እባላለሁ። በዚህ ክፍል የሰዎችን ዕድሜ እንዴት መጠየቅ እንደሚቻል ይማራሉ።
እስኪ ሁለት ሰዎች ዕድሜ ሲጠያየቁ ያዳምጡ።
Gina
How old are you?
Tom
I’m thirty-five. How about you?
Gina
I’m twenty-three.
ይህ አስቸጋሪ ቢሆንብዎት ብዙም ጭንቀት አይግባዎት፤ ውይይቱን ከፋፍለን እንዲለማመዱት እናግዝዎታለን።
በመጀመሪያ ጂና ቶምን ‘ዕድሜህ ስንት ነው?’ ‘How old are you?’ ስትል ጠይቃዋለች። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
How old are you?
ከዚያም ቶም ‘ሰላሳ አምስት ዓመቴ ነው’ ‘I’m thirty-five’ ሲል መልሷል። ‘I’m…’ የሚለውን አገላለፅ የሰዎችን ዕድሜ ለመናገር እንጠቀምበታለን። ከአስራ አንድ እና አስራ ሁለት ‘eleven and twelve’ በኋላ፥ ከአስራ ሶስት እስከ አስራ ዘጠኝ ያሉት ቁጥሮች ‘teen’ የሚጨርሱ ናቸው። ስለዚህም እንዲህ እንላለን፤
አስራ አንድ Eleven
አስራ ሁለት Twelve
አስራ ሶስት Thirteen
አስራ አራት Fourteen
አስራ አምስት Fifteen
አስራ ስድስት Sixteen
አስራ ሰባት Seventeen
አስራ ስምንት Eighteen
አስራ ዘጠኝ Nineteen
ሃያ አምስትን ለመግለፅ ‘ሃያ’ ‘twenty’ ን ከ‘አምስት’ ‘five’ ጋር እናጣምረዋለን፤ ስለዚህም ‘twenty-five’. እንላለን። አርባ ሰባትን ለመግለፅ ‘አርባ’ ‘forty’ እና ‘ሰባት’ ‘seven’ ን እናጣምርና ‘forty-seven’ እንላለን። ከሃያ እስከ ዘጠና ያሉት ቁጥሮች እንደሚከተሉት ናቸው፤
ሃያ Twenty
ሰላሳ Thirty
አርባ Forty
ሃምሳ Fifty
ስድሳ Sixty
ሰባ Seventy
ሰማንያ Eighty
ዘጠና Ninety
በመቀጠል ቶም ‘ሰላሳ አምስት ዓመቴ ነው’ ‘I am thirty-five’. ሲል መልሷል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
I’m thirty-five.
ቶም ከዚያ ‘አንችስ?’ ‘How about you?’ በማለት ተመሳሳዩን ጥያቄ አዙሮ ጠይቋል። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
How about you?
በመጨረሻ ጂና ለቶም ሃያ ሶስት ዓመቴ ነው ‘I’m twenty-three’ ብላ መለስችለት። ያዳምጡና ሐረጉን ደግመው ይበሉ።
I’m twenty-three.
በጣም ጥሩ- አሁን የተለያዩ ሰዎች ስለዕድሜያቸው ሲነጋገሩ በማዳመጥ እርስዎ ምን እንዳሉ ያጣሩ።
How old are you?
I’m seventeen. How about you?
I’m sixteen.
How old are you?
I’m fifty-eight. How about you?
I’m seventy-four.
How old are you?
I’m forty-two. How about you?
I’m twenty-six.
በጣም ግሩም! እስኪ እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንዳስታወሱ እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይበሉ።
ዕድሜህ ስንት ነው?
How old are you?
ሰላሳ አምስት ዓመቴ ነው። አንችስ?
I’m thirty-five.
እርስዎስ?
How about you?
ሃያ ሶስት ዓመቴ ነው።
I’m twenty-three.
በጣም ጥሩ፤ እስኪ አሁን የዛሬዎቹን አገላለፆች ለማስተዋል ሙሉውን ውይይት ያዳምጡ።
Gina
How old are you?
Tom
I’m thirty-five. How about you?
Gina
I’m twenty-three.
በጣም ጥሩ! አሁን በእንግሊዝኛ የሰዎችን ዕድሜ መጠየቅ ይችላሉ። የተማሩትን ነገር መለማመድን አይዘንጉ። ጓደኛ ይፈለጉና አግብተው መሆን ያለመሆኑን በእንግሊዝኛ ይጠይቋቸው። ጥያቄውን ላቀረበው ሰው መለሰው መጠየቅንም አይርሱ። ለተጨማሪ የዕለት ተዕለት እንግሊዝኛ በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!
Check what you’ve learned by choosing the correct answer to the question.
ለጥያቄው ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ ምን ያህል እንደተማሩ ይፈትሹ።
How old are you?
3 Questions
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
ዕድሜየ/ዕድሜው/ዕድሜዋ...Question 1 of 3
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
ሶስት ሆሄያትQuestion 2 of 3
ድጋፍ
Activity
Choose the correct answer.
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ።
ፍንጭ
የቁጥሩን መደምደሚያ በአንክሮ ያጢኑ።Question 3 of 3
Excellent! Great job! መጥፎ እድል ነጥብ አስመዝግበዋል :
Join us for our next episode of Essential English, when we will learn more useful language and practise your listening skills.
ተጨማሪ ጠቃሚ የቋንቋ መሰረታዊያን ለመማር እና የማዳመጥ ክህሎትዎን በመለማመድ ለማዳበር በቀጣዩ መሰረታዊ እንግሊዝኛ ክፍላችን ይጠብቁን።
የ Facebook ቡድናችንን ይቀላቀሉ!
Session Vocabulary
How old are you?
ዕድሜህ/ዕድሜሽ ስንት ነው?I’m ______.
ነው።How about you?
አንተስ/አንችስ??eleven
አስራ አንድ
twelve
አስራ ሁለት
thirteen
አስራ ሶስት
fourteen
አስራ አራት
fifteen
አስራ አምስት
sixteen
አስራ ስድስት
seventeen
አስራ ሰባት
eighteen
አስራ ስምንት
nineteen
አስራ ዘጠኝ
twenty
ሃያ