የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ሕይወት በምስል

የፎቶው ባለመብት, Annie Leibovitz

ንግሥት ኤልዛቤጥ ዘመናቸውን በሙሉ ለሕዝብ አገልግሎት አውለዋል። እነዚህ ታሪካዊ ምስሎች ከልጅነት ጊዜያቸው አንስቶ እስከ ንግሥና ዘመናቸው ያለፉበትን በጥቂቱ ያሳያሉ።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ኤልዛቤጥ አሌክሳንደር ሜሪ ዊንዘር የተወለዱት እአአ 1926 ለንደን ከተማ ነበር። ኤልዛቤጥ የዮርኩ አልጋ ወራሽ አልበርት እና የኤልዛቤጥ ቦውስ-ሊዮን የመጀመሪያ ልጅ ናቸው። ንግሥት ኤልዛቤጥ በወላጆቻቸው እቅፍ ሆነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በታዳጊነት ዘመናቸው ንግሥናው ወደእርሳቸው የሚመጣ አይመስልም ነበር። ንግሥት ኤልዛቤጥ እአአ 1929።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ይሁን እንጂ ኤልዛቤጥ ገና ልጅ ሳሉ ኃላፊነትን ይወስዱ ነበር። የወቅቱ ልዕልት ኤልዛቤጥ በዊንዘር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኤልዛቤጥ እና ታናሽ እህታቸው ማርጋሬት ሮዝ ትምህርት የተማሩት በቤት ውስጥ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ንግሥናውን ጥለው ከወጡ በኋላ፣ የኤልዛቤጥ አባት ንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ ንግሥናውን ሲቀበሉ ኤልዛቤጥ አልጋ ወራሽ ሆኑ።

የፎቶው ባለመብት, Topical Press Agency / Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ኤልዛቤጥ እና እህታቸው ማርጋሬት ወደ ዊንዘር ተወስደው ነበር። ይህ ምስላቸው በቢቢሲ የልጆች ዝግጅት ላይ ቀርበው መልዕክት ሲያስተላለፉ የተነሳ ነው።

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, በጦርነቱ ወቅት ወጣቷ ልዕልት ኤልዛቤጥ ጦሩን በመቀላቀል መኪና ማሸከርከር እና መጠገንን ተምረው ነበር። ይህ ምስል እአአ 1940ዎቹ የመኪና ጎማ ሲቀይሩ ያሳያል።

የፎቶው ባለመብት, Bert Hardy / Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1947 ላይ ፊሊፕ ሞንትባተንን አገቡ። ሞንትባተን የኤደንብራ አልጋወራሽ ሆነዋል። የልዕልት ኤልዛቤጥ እና የፊሊፕ ሞንትባተን የሠርግ ሥነ-ሥርዓት በዌስትሚኒስተር አቤይ እአአ 1947።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, የመጀመሪያ ልጃቸው ቻርለስ የተወለደው እአአ 1948 ነበር። ሁለተኛ ልጃቸው ደግሞ 1950 ላይ ተወልዳለች። ምስል ንግሥት ኤልዛቤጥ ከአሁኑ ንጉሥ ቻርለስ ጋር።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ኤልዛቤጥ ከእናቷ ጋር ቅርብ ግንኙነት ነበራቸው። ምስሉ እአአ 1951 በሠርግ ሥነ-ሥርዓት ላይ በታደሙበት ወቅት የተነሳ ነው።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ኤልዛቤጥ እአአ 1952 ላይ የታመሙ አባታቸውን በመተካት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝንት ከአገር ውጪ ጉብኝት ጀመሩ። ንግሥቲቱ በኬንያ ጉብኝት ላይ ሳሉ የአባታቸው ሕይወት አልፏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የአባታቸውን ሞት ተከትሎ ኤልዛቤጥ በፍጥነት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ተመለሱ። በዚህ ወቅት ኤልዛቤጥ ዕድሜያቸው ገና 25 ዓመት ነበር።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, የንጉሥ ጆርጅ የቀብር ሥነ-ሥርዓት። በዚህ ምስል ላይ የንጉሡ እናት ንግሥት ሜሪ ከፊት ለፊት ሆነው ይታያሉ።

የፎቶው ባለመብት, Universal History Archive

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1953 ላይ ንግሥት ኤልዛቤጥ በዌስትሚኒስቴር አቤይ የንግሥና ሥነ ሥርዓታቸው ሲካሄድ።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ከንግሥና ሥርዓቱ በኋላ ንግሥት ኤልዛቤጥ እና የኤደንብራው ዱክ ባኪንግሃም በረንዳ ላይ ቀርበው ለሕዝቡ ሰላምታ ሰጥተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ እአአ 1957 ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፓሪስ ፈረንሳይ ባቀኑበት ወቅት።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥቲቱ እአአ 1957 የመጀሪያቸው የሆነውን የገና በዓል ንግግር አደረጉ። ከዚያ በኋላ አስከ ህልፈታቸው ድረስ የገና በዓል መልዕክቶችን ለሰባት አስርት ዓመታት አስተላለፈዋል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ እአአ 1958 ለንደን ከተማ።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ ከሴት ልጃቸው ልዕልት አን ጋር በዊንዘር ቤተ-መንግሥት።

የፎቶው ባለመብት, Mirrorpix / Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1966 እንግሊዝ ምዕራብ ጀርመንን 4-2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዓለም ዋንጫን ስታሸንፍ ንግሥት ኤልዛቤጥ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል የዋንጫ ሽልማቱን ሰጥተው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ንግሥቲቱ እአአ 1966 የድንጋይ ከሰል ክምር ተደርምሶ 144 ሰዎች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ አደጋው ወደደረሰበት የዌልስ አበርፋን መንድር ለጉብኝት ሄደው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Mirrorpix / Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1969 የንጉሣውያን ቤተሰብ ሕይወትን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ተላልፎ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ ከልጃቸው ልዑል ቻርለስ ጋር

የፎቶው ባለመብት, Lichfield via Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1972 ላይ ንግሥቲቱ የጋብቻቸውን የብር ኢዩቤልዩን ለማክበር የተነሱት ፎቶግራፍ።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥቲቱ ብዙ ጊዜ ከውሾቻቸው ጋር ሆነው በአደባባይ ይታያሉ።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1977 ላይ የንግሥቲቱ የ25ኛ ዓመት የንግሥና በዓል በድምቀት ተከብሯል። በዓለ ሲመታቸውን ተከትሎ በመላው አገሪቱ ያደረጉት ጉብኝት ብዙዎች አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ገልጸዋል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, በንግሥና በዓላቸው ወቅት ኤልዛቤጥ በ10 ሳምንታት 36 አገራትን ጎብኝተዋል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥቲቱ እና ባለቤታቸው ወደ ባርቤዶስ በተጓዙበት ወቅት ኮንኮርድ አውሮፕላን ዝቅ ብሎ ሲበር ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላቱ እጃቸውን እያወዛወዙ ሰላምታ ሲሰጡ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1981 የንግሥት ኤልዛቤጥ የመጀመሪያ ልጅ ቻርለስ፣ ሌዲ ዳያና ስፔንሰርን አገባ። ቻርለስ እና ዳያና ሁለት ልጆችን ወልደዋል። ዊሊያም እና ሃሪ። ዳናያ እአአ 1997 በመኪና አደጋ ፓሪስ ውስጥ ሕይወቷ አልፏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ እአአ በ1992 በዊንዘር ቤተ-መንግሥት የእሳት አደጋ መከሰቱን እንዲሁም የሦስት ልጆቻቸው ትዳር መፍረሱን ተከትሎ ዓመቱን በመልካም እንደማያስቡት ተናግረዋል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, እአአ 1997 ላይ የዳያናን ሞት ተከትሎ ንግሥቲቱ በአደባባይ ሳይታዩ መቆየታቸው ቁጣን ቀስቅሶባቸው ነበር። ከዚያም ሕዝቡ ሐዘኑን ለመግለጽ የስቀመጠውን የአበባ ጉንጉን ለመመልከት ከቤተ-መንግሥቱ ደጃፍ በአደባባይ ታይተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 2000 ላይ የንግሥት ኤልዛቤጥ እናት 100ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን አክብረዋል። በዚህ ምስል ላይ የንግሥቲቱ እናት በሁለት ልጆቻቸው መካከል ሆነው ይታያሉ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, እአአ 2002 ላይ ንግሥት ኤልዛቤጥ ታናሽ እህታቸውን ልዕልት ማርጋሬትን በሞት አጥተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የንግሥት ኤልዛቤጥ 50ኛ ዓመት የንግሥና በዓል በድምቀት ተከብሯል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, እአአ 2005 ላይ ንግሥት ኤልዛቤጥ የመጀመሪያ ልጃቸው ቻርለስን ለሁለተኛ ጊዜ ሞሸረዋል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, ንግሥት ኤልዛቤጥ የፈረስ ግልቢያ ውድድር የሚወዱት ስፖርት ነበር። ኤስትሜት በተባለው ፈረሳቸው 207ኛውን ዶልድ ካፕን ማሸነፍ ችለዋል። ይህም ለንግሥቲቱ እና ለውድድር ኃላፊው ጆን ዋረን ትልቅ ፈንጠዝያ ፈጥሯል።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, እአአ መስከረም 9 ቀን 2015 ኤልዛቤጥ ለ23,226 ቀናት፣ ለ16 ሰዓታት ከ30 ደቂቃ ገደማ ንግሥት በመሆናቸው ከቅመ አያታቸው ንግሥት ቪክቶሪያ በንግሥና በመቆየት ለመብለጥ ቻሉ። በዕለቱ ስኮትላንድ በመገኘት አዲስ የባቡር መንገድ አስጀመሩ።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, እአአ 2016 ላይ ንግስቲቱ ከሌሎች የንጉሣዊያን የቤተሰብ አባላት ጋር የልደት በዓላቸውን ለማክበር በይፋ ታይተው ነበር። በዚያ ዓመት መጀመሪያ ላይ 90 ዓመት ደፍነው ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የኤድንበራው መስፍን ጡረታ ከወጡ በኋላ ንግሥቲቱ ብቻቸውን ሕዝባዊ ተግባራቸውን መወጣት ቀጥለዋል። ንግሥቲቱ እአአ በ2018 በሮያል ዊንዘር የፈረስ ውድድር ላይ ፈረሳቸው ስፓርክለር ሲወዳደር እየተመለከቱ።

የፎቶው ባለመብት, Chris Allerton / SussexRoyal

የምስሉ መግለጫ, የቤተሰብ ቁጥር መጨመር ለንግሥቲቱ ደስታ ነበር። በዚህ ምስል ላይ የሰሴክስ አልጋ ወራሽ እና ሶፋኒት ከልጃቸው አርቺ ጋር ይታያሉ። በቤተሰቡ ዙሪያ ቀጣይ ችግሮች ነበሩ። ልዑል አንድሪው ከአሜሪካዊው ባለሃበት እና በወሲብ ቅሌት ጥፋተኛ ከተባሉት ጄፍሪ ኤፕስታይን ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንዲሁም ልዑል ሃሪ በንጉሣዊ ቤተሰብ ውስጥ በነበረው ሕይወት ደስተኛ አለመሆን ተጠቃሾች ናቸው።

የፎቶው ባለመብት, PA Media

የምስሉ መግለጫ, የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ባለቤት ልዑል ፊሊፕ በ99 ዓመታቸው እአአ 2021 አረፉ። ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ በትዳር አብረው ቆይተዋል። በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በነበረው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ብቻቸውን ተቀመጠው የሚታዩበት የንግሥቲቱ ምስል በተመሳሳይ መልኩ የሚወዷቸውን ያጡ ሰዎችን ሁኔታ የሚያሳይ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Duchess of Cambridge

የምስሉ መግለጫ, ንግሥቲቱ አራት ልጆችን፣ ስምንት የልጅ ልጆችን እና 12 የልጅ ልጅ ልጆችን ለማት በቅተዋል።

ሁሉም ምስሎች የባለቤትን መብት የጠበቀ ነው።