በአዲስ አበባ ለመንግሥት እና ለመከላከያ ድጋፍ ለማሳየት የተደረገው ሰልፍ በምስል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ትናንት ለመንግሥት ድጋፍ ለመግለጽ በተደረገው ሰልፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ አደባባይ ወጥቷል።

ትናንት ዕሁድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በአዲስ አበባ ከተማ የፌደራሉ መንግሥት ከአማጺው ቡድን ህወሓት ጋር በሚያደርገው ውጊያ ለመንግሥት ያለው ድጋፍ ለመግለጽ አደባባይ ወጥቷል።

በመንግሥት እና በህወሓት መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ባለፈው ሳምንት አንድ ዓመት ማስቆጠሩ ይታወሳል።

እየተካሄደ ባለው ጦርነት በርካታ ሰዎች ስለመገደላቸው እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ የሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂ መሆናቸው በተደጋጋሚ ተዘግቧል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ግጭቱ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያፈናቀለ ሲሆን፤ በትግራይ ወደ 400ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ረሃብ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ።

የፎቶው ባለመብት, Google

የምስሉ መግለጫ, በትናንቱ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በርካቶች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ግጭቱን በተመለከተ ሐሰተኛ መረጃ ያሰራጫሉ ሲሉ ብስጭታቸውን ገልጸዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋ ነዋሪ ከአማጺያኑ ጋር በሚደረገው ጦርነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ባለፉት ቀናት የህወሓት አማጺያን እንደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ያሉ ቁልፍ የደቡብ ወሎ ከተሞችን መቆጣጠር ችለዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጫናዎች በርትተውባቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በቅርቡ አማጺያኑን "ለመቅበር" አቅም ያለው ዜጋ ሁሉ ነፍጥ እንዲያነሳ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አጎራባች ክልሎች እየተስፋፋ ያለው ጦርነት እንዲቆም መንግሥታት እና የረድኤት ድርጅቶች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

ሁሉም ምስሎች የባለቤትነት መብታቸው የተጠበቀ ነው።