የኢሬቻ አከባበር በምሥል

የንባብ ጊዜ: 4 ደቂቃ

የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።

የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፤ በቢሾፍቱ ከተማ ደግሞ የሆራ ሃር-ሰዲ በዓላት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በታደመበት ይከበራሉ።

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን መገባደድ ተከትሎ ለፈጣሪ ምሥጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም መጪው ዘመን በጎ እንዲሆን ፈጣሪን የሚለምንበት ነው።

ዛሬ በአዲስ አበባ እየተከበረ ያለውን የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በምሥል እንደሚከተለው አጠናቅረናል።

የምስሉ መግለጫ, በበዓሉ ላይ የተገኙ ሃደ ሲንቄዎች
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን መገባደድ ተከትሎ ለፈጣሪ ምሥጋና የሚያቀርብበት እንዲሁም መጪው ዘመን በጎ እንዲሆን የሚለምንበት ነው
የምስሉ መግለጫ, ወጣቶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው ታይተዋል
የምስሉ መግለጫ, በበዓሉ ላይ የተገኙ አባ ገዳዎች
የምስሉ መግለጫ, የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል
የምስሉ መግለጫ, የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር ቆይቷል
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፤ በቢሾፍቱ ከተማ ደግሞ የሆራ ሃር-ሰዲ በዓላት ይከበራሉ
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ ማለት ዋቃ (ፈጣሪ) የፈጠረውን ማመስገን ማለት ነው
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ የዘመን መለወጫ በዓልም ነው
የምስሉ መግለጫ, ማኅበራዊ ደረጃ እና የዕድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር ቆይቷል
የምስሉ መግለጫ, በኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላሸጋገረው አምላክ አምላክ ምስጋና ያቀርባል
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ በዓል ሁለት ጊዜ ይከበራል
የምስሉ መግለጫ, ኢሬቻ የሰላም እና እርቅ በዓል ይባላል
የምስሉ መግለጫ, 'ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያጸደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመስግንሃለን' በማለት እርጥብ ነገር ተይዞ ይወጣል
የምስሉ መግለጫ, የኢሬቻ በዓልን ለማክበረ የሚወጣ ታዳሚ እንደ ሳር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይይዛል
የምስሉ መግለጫ, የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ
የምስሉ መግለጫ, የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ