የደመራ አከባበር ከኢትዮጵያ እስከ ኬንያ

የመስቀል ደመራ በዓል እንዴት ተከበረ? ዘጋቢዎቻችን ከኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ፣ በአዲግራት እና በባህር ዳር ያለውን ድባብ በፎቶ አስቃኝተውናል። በኬንያ መዲና ናይሮቢም በዓሉ በምን መንገድ እንደተከበረ በፎቶግራፍ ሰንደናል።

መስቀል በባህር ዳር

የምስሉ መግለጫ, በባህር ዳር ከተማ የመስቀል ደመራ በዓልን ለማክበር አደባባይ ከወጡ የሐይማኖት አባቶች መካከል አንዱ
የምስሉ መግለጫ, በባህር ዳር ከተማ የመስቀል በዓል አከባበር ላይ በገና የሚደረድሩ ታዳጊዎች ነበሩ
የምስሉ መግለጫ, በባህር ዳር ከተማ ሕዝበ ምዕመን የመስቀል ደመራ በዓልን ሲታደም
የምስሉ መግለጫ, የባህር ዳር ከተማ የመስቀል በዓል ላይ የተገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች
የምስሉ መግለጫ, በባህር ዳር ከተማ ሕዝበ ምዕመን የመስቀል ደመራ በዓልን ሲታደም

መስቀል በአዲስ አበባ

የምስሉ መግለጫ, አዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የደመራ በዓል ሲከበር
የምስሉ መግለጫ, በመስቀል አደባባይ በዓሉን ለማክበር ከተገኙት መካከል በተሸለመ ፈረስ ላይ የተቀመጡት ይገኙበታል
የምስሉ መግለጫ, በመስቀል አደባባይ ስለ በዓሉ ሀይማኖታዊ ዳራ የሚያሳይ ትዕይንት ቀርቧል

መስቀል በአዲግራት

የምስሉ መግለጫ, የመስቀል ደመራ በዓል በአዲግራት ከተማ ሲከበር
የምስሉ መግለጫ, የአዲግራት ከተማ የመስቀል ደመራ አከባበር በጠጅ የታጀበ ነበር
የምስሉ መግለጫ, የመስቀል ደመራ በዓል በአዲግራት ከተማ ሲከበር
የምስሉ መግለጫ, በአዲግራት ከተማ የኩናማ ብሔረሰብ ተወላጆች ባህላዊ ውዝዋዜ አቅርበዋል

መስቀል በናይሮቢ

የምስሉ መግለጫ, በናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር
የምስሉ መግለጫ, በናይሮቢ የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር መዘምራን ወረብ አቅርበዋል
የምስሉ መግለጫ, በናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል ሲከበር
የምስሉ መግለጫ, በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ለበዓሉ ታዳሚዎች ንግግር አድርገዋል
የምስሉ መግለጫ, ነዋሪነታቸውን በናይሮቢ ያደረጉ ታዳጊዎች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል
የምስሉ መግለጫ, በናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከብሯል