የአፍሪካን ሳምንት በምስል፡ እሳትና በረዶ

በዚህ ሳምንት ከተለያዩ የአፍሪካ ገራት እና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚገኙ አፍሪካውያን የተሰበሰቡ ምርጥ ምስሎ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, የኬኒያ የአክሮባት ቡድን አባላት በናይሮቢ እሳት የመትፋት ትርዒት ሲያቀርቡ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, ሁለት ወጣት የዳምቤ ቦክሰኞች በሌጎስ የጦረኞች ውድድር ላይ ሲቧቀሱ፤- ይህ ባሕላዊ ጨዋታ በሰሜን ናይጄሪያ የሐውሳ ጎሳ አባላት የሚዘወተር ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኬኒያዊቷ ተዋናይት ሉፒታ ኒዮንጎ እሁድ ዕለት በተካሄደው የኦስካር ሽልማት ላይ ፀጉሯን በሩዋንዳ ባህላዊ አጊያጊያጥ አስውባ

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በምዕራብ አውሮፓ የተከሰተው ወቅቱን ያልጠበቀው ቀዝቃዛ አየር በዚህ ሳምንት በሞሮኮው አትላስ ተራሮች ላይም በረዶ ፈጥሮ ነበር

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, እረቡ እለት በሴራሊዮን የተደረገው ምርጫ በአንዳንድ ቦታዎች ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ውጭ በቡዙ ቦታዎች ሰላማዊ ነበር

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, እነዚህ ሴሪዮላውያን ከአሸዋ እና ጭቃ ወርቅ ለይቶ ለማውጣት ጠንክረው እየሠሩ ነው

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ከሆሎት ስደተኞች ማቆያ ሲወጡ ለመታሰቢያ ፎቶ ሲነሱ

Images courtesy of AFP, Reuters, PA and Getty Images