ባህሬን የኢራን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 450 ድሮኖችን ማክሸፏን አስታወቀች

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ባሕሬን የኢራን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ምን ያህል የአየር ጥቃቶችን ማክሸፏን ዛሬ ይፋ አድርጋለች።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከኢራን የተወነጨፈ 188 ሚሳዔሎችን እና 453 የድሮን ጥቃቶች “ማክሸፏን እና ማውደሟን” አስታውቃለች።
የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በዛሬው ዕለት ብቻ 56 ድሮኖችን እና 23 ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ማክሸፏን አስታውቋል።
ከአምስት ሳምንት በፊት ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 498 ባሌስቲክ ሚሳዔሎችን እና 23 ክሩዝ ሚሳዔሎችን እንዲሁም 2ሺህ 141 ድሮኖችን ማክሸፉን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባጋራው መረጃ ላይ ይፋ አድርጓል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶም ሁለት የአገሪቱ ጦር አባላት፣ አንድ የውጭ አገር ባለሙያ እና 10 ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል።
217 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ስለ ኢራን ጥቃቶች የዘገቡ መገናኛ ብዙኃን ይፋ ያደረጉት መረጃ እንደሚያሳየው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከፍተኛ ዒላማ ሆና ቆይታለች።
















