ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለጠፈ እና ኢራን ውስጥ የወደቀው የአሜሪካ ተዋጊ አውሮፕላን ስብርባሪ የሚያሳይ ምሥል የተከሰከሰው “ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል” የጦር ጄት እንደሆነ ያመለክታል።
የዚህ ጄት ዝርያዎች ከአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበረ ቢሆንም “ኤፍ-15ኢ” ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀው በ1988 ነው። የአንዱ ጄት ዋጋ 100 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ነው።
እንዲህ ዓይነቶቹ ተዋጊ ጄቶች የሚሠሩት ከአየር
ወደ ምድር እንዲሁም የአየር ለአየር ተልዕኮዎች እንዲወጡ ተደርጎ ነው።
የአሜሪካው ጄት ኢራን ውስጥ ድሮኖችን እና ክሩዝ ሚሳዔሎችን
ለመምታት ለመከላከያ የአጸፋ የአየር ጥቃት ተጉዞ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
ጄቱ ከአየር ወደ ምድር ጥቃት በሚፈጽምበት ወቅት
ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ዒላማው ላይ ጨረር የማስቀመጥ እንዲሁም በጂፒኤስ የሚመሩ ትክክለኛ ዒላማ መቺ ተተኳሾችን እና ሌሎች ቦንቦችን
የመያዝ አቅም አለው።
የጦር አውሮፕላኑ ሁለት ሰዎችን መያዝ ይችላል።
ጄቱን የሚያበርረው ፓይለት ከፊት የሚቀመጥ ሲሆን የመሣሪያ ሥርዓት መኮንኑ ደግሞ የኋለኛው መቀመጫ ላይ ይሆናል።
የመሣሪያ ሥርዓት መኮንኑ ከፊት ለፊቱ አራት
ስክሪኖች ይኖሩታል። ዒላማዎችን የመምረጥ እና ለጥቃት ዒላማው ተገቢ የሆነው መሣሪያ በአግባቡ መዘጋጀቱን የማረጋገጥ ኃላፊነቶችን
ይወጣል።
ተዋጊ ጄቱ ሁለት ሰዎችን የሚጭን መሆኑ የሥስራ
ክፍፍል እንዲኖር ያስችላል። በተለይም አብራሪው ከጠላት ለማምለጥ በሚሞክርበት አስጨናቂ የአየር ከባቢ ውስጥ ጠቃሚ ነው።
የአሜሪካውን ተዋጊ ጄት እንዲወድቅ ያደረገው ትክክለኛ ነገር ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር
ያዳግታል።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ እንደገለጸው መትቶ ጥሎት ከሆነ ጄቱን የመታው ከምድር ወደ አየር የተወነጨ ሚሳዔል የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው።
“በኢንፍራ ሬድ’ ጨረር የሚመራው የአጭር ርቀት ሚሳዔል
ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላል። በቶሎ ማዘዋወር የሚቻል በመሆኑም ኢራን ውስጥ በሚካሄዱ ዘመቻዎች ላይ ከፍተኛ ስጋትን መደቀኑን
ቀጥሏል።
ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተዋጊ ጄቶች የሚቃጠል ጭስ በመልቀቅ
ከምድር ላይ የተነሳው ሚሳዔል ዒላማዋን እንዲስት በማድረግ ራሳቸውን ለመከላከል ይሞክራሉ።
በዚህ ጦርነት ውስጥ የአሜሪካ ወታደራዊ አዛዦች
በኢራን የተለያዩ ክፍሎች ላይ የአየር የበላይነት እንዳላቸው ሲናገሩ ነበር።
ነገር ግን ጄቱ ተመትቶ እንደወደቀ የሚረጋገጥ ከሆነ አሁንም
ኢራን ለአሜሪካ የጦር ጄቶች ምን ያህል አደጋ መጋረጥ እንደምትችል ያሳያል።