14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በፎቶ

14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሮ ውሏል።

የምስሉ መግለጫ, 14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል።
የምስሉ መግለጫ, የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ማክበር የተጀመረው በ1998 ዓ.ም ነው።
የምስሉ መግለጫ, በዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን አከባበር ላይ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴንና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።
የምስሉ መግለጫ, የዘንድሮው በዓል መሪ ቃል "ሕገ መንግሥታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም" የሚል ነው
የምስሉ መግለጫ, ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር አዘጋጅነት ይካሄዳል።
የምስሉ መግለጫ, በበዓሉ ላይ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባህልና የአኗኗር ዘይቤያቸውን የሚያሳዩ ትዕይንቶችን አቅርበዋል።
የምስሉ መግለጫ, ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት "የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገርና በውይይት መፍታት ይገባል" ብለዋል።