የሲዳማ ዞን ሕዝበ-ወሳኔ በምስል

ዛሬ የሲዳማ ዞን፤ ክልል መሆን አሊያም በደቡብ ክልል ስር መቆየትን በተመለከተ ሕዝበ-ወሳኔ የሚከናወንበት ቀን ነው። መራጮች ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፅ እየሰጡ ነው። ምርጫው እስከ ምሽት 12፡00 ሰዓት ይዘልቃል። ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሕዝበ-ውሳኔው ለመሳተፍ ተመዝግበዋል።

የምስሉ መግለጫ, ዕድሜያቸው የገፋ ሰዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል።
የምስሉ መግለጫ, ንጋት 12፡00 ሰዓት የጀመረው ምርጫ ምሽት 12፡00 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የምስሉ መግለጫ, ሐዋሳ የሚገኙት የቢቢሲ ባልደረባዎች ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ እና የፀጥታ አስከባሪዎች በየቦታው በተጠንቀቅ እንደቆሙ መመልከት ችለዋል።
የምስሉ መግለጫ, ምርጫው እስከ ምሽት 12፡00 ሰዓት ይዘልቃል።
የምስሉ መግለጫ, ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሕዝበ-ውሳኔው ለመሳተፍ ተመዝግበዋል።
የምስሉ መግለጫ, መራጮች ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በምርጫ ጣብያዎች ተገኝተው ድምፅ መስጠት እንደጀመሩ በሥፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢዎች ቡድን ታዝቧል።
የምስሉ መግለጫ, የምርጫው ውጤት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይፋ እንደሚሆን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የምስሉ መግለጫ, ሲዳማ ከደቡብ ከልል ጋር እንድትቆይ የሚፈልጉ ጎጆ፤ ሲዳማ ዞን ክልል እንትሆን የሚፈልጉ ደግሞ ሻፌታን ይመርጣሉ
የምስሉ መግለጫ, የሲዳማ ሕዝብ ላለፉት ዓመታት የክልልነት ጥያቄ ሲያቀርብ ነበር
የምስሉ መግለጫ, ባለፈው ሐምሌ በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሐዋሳ እና ሌሎች ከተሞች ግጭት ተነስቶ ሕይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል
የምስሉ መግለጫ, የሲዳማ ክልል ይሁን ጥያቄ ዋነኛ አቀንቃኝ የወጣቶች ቡድን 'ኤጄቶ' በመባል ይታወቃል